አዲስ አበባ —
- “ኢትዮጵያ ላይ እየተደረገ ያለው ጫና፣ በሶማሊያ ጊዜ ከነበረው ጋር ይመሳሰላል” - የፖለቲካ ሳይንስ ምሁር
ሀገራቸው በተመሳጠረ ዓለም አቀፍ የትችት ወይም የነቀፌታ ማዕበል ውስጥ እያለፈች መሆኑን የገለፁት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ አፍሪካዊያን ከኢትዮጵያ ጎን እንዲቆሙ ጥሪ አቅርበዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሰሞኑን ለበጎ ፈቃደኛ ወጣቶች ባደረጉት ንግግርም ኢትዮጵያ አሁን ያለችበት ሁኔታ ትንሹም፣ ትልቁም ተረባርቦ የተነሳባት ጊዜ መሆኑን ገልፀው፤ ሀገራቸው ግን በማንም ጫና እንደማትቆም አስታውቀዋል።
አንድ አንጋፋ የፖለቲካ ሳይንስ ምሁር እንዳሉት ደግሞ አሁን በኢትዮጵያ ላይ እየተደረገ ያለው ጫና ሃገሪቱ ካለፈችበት ሌላ የታሪክ አጋጣሚ ጋር ይመሳሰላል።
የአሁኑ ጫና አንዱ ምክንያትም የሕዳሴው ግድብ መሆኑን እኝሁ ምሁር ያምናሉ።
ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።
Your browser doesn’t support HTML5