በኢትዮጵያ የሰብዓዊ ረድዔት ምላሽ ቀጥሏል

  • ቆንጂት ታየ

Your browser doesn’t support HTML5

በኢትዮጵያ የሰብዓዊ ረድዔት ምላሽ ቀጥሏል

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ቢሮ /ኦቻ/ ጦርነት ለተካሄደባቸው የትግራይ እና የአፋር ክልሎች ተጨማሪ የምግብ እርዳታ ሲያደርስ መቆየቱን አስታውቋል፡፡ ሆኖም ተቋሙ በዚህ ሳምንት ባወጣው ሪፖርቱ በሀገሪቱ ያለው የተመጣጠነ ምግብ እጥረት በአሳሳቢ ደረጃ ከፍተኛ መሆኑን ገልጿል፡፡

የረድዔት ሠራተኞች ለመድረስ ያልቻሉባቸው አካባቢዎች እንዳሉም ተመድ አስታውቋል።

ባለፈው ኅዳር ወር በፌዴራል መንግሥቱ እና በትግራይ ክልል ባለሥልጣናት መሃከል የሰላም ስምምነት የተፈረመ ቢሆንም አሁንም ወደ አንዳንድ አካባቢዎች እርዳታ ለማድረስ ችግር እንዳለ የመንግሥታቱ ድርጅት ገልጿል፡፡

/ሙሉውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ/