ሁለት ዓመቱን ሊደፍን የተቃረበውን በኢትዮጵያ ፌዴራል መንግሥትና ትግራይ ክልልን እያስተዳደረ ባለው ህወሓት መሃከል ያለውን ግጭት በዘላቂነት የሚያስቆም የሰላም ድርድር ለማድረግ ዝግጅት እየተደረገ ሲሆን በጦርነቱ ከባድ ውድመት የደረሰባት የአፋር ክልሏ አብዐላ ከተማ ነዋሪዎችና የሚሊሽያ አባላት ለሰላም ዝግጁ መሆናቸውን ይናገራሉ።
ሁኔታውን የሚከታተሉ ተንታኞች ግን ሰላም እንዲህ በቀላሉ ላይጨበጥ ይችላል ሲሉ ሥጋታቸውን ገልፀዋል።
በሌላ በኩል በአፋር ክልል በረሃብ ስቃይ ውስጥ የሚገኙ ሰዎች ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ለእርዳታ እንዲደርስላቸው እየተማፀኑ ነው።
/ዘገባው የቪኦኤ ዘጋቢ ሄንሪ ዊልኪንስ እና የአዣንስ ፍራንስ ፕሬስ ነው። ሙሉውን ከተያያዘው ፋይል ያዳምጡ/