እንግሊዝ በፕሬዚዳንት ፑቲን የአገዛዙ ባለሥልጣናት ንብረት ላይ ማዕቀብ ለመጣል ቃል ገባች

  • ቪኦኤ ዜና

የሩስያ ኢምባሲ ለንደን

የእንግሊዝ ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን ትላንት እሁድ በሰጡት መግለጫ ሩሲያ በዩክሬን ወረራ የምታካሂድ ከሆነ እንግሊዝ ውስጥ ሀብትና መዋዕለ ንዋይ ባላቸው በሩሲያው ፕሬዚዳንት ፑቲንና የአገዛዙ ባለሥልጣናት ላይ በቀላሉ ማዕቀብ መጣል የሚያስችለውን ህግ ከወዲሁ ለማዘጋጀት እያቀደች መሆኑን ቃል በመግባት አስታወቀዋል፡፡

ሩሲያ በለንደን ከሁለት ቢሊዮን ዶላር በላይ ንብረት ያላት መሆኑን በበርሊን ያለው የዓለም አቀፉ የግልጽነትና ጸረ ሙስና ምርምር ተቋም አስታውቋል፡፡

የጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ውሳኔ ፕሬዚዳንት ባይደን እና ሌሎች ምዕራባውያን አገሮች ሩሲያ ዩክሬንን ብትወር ጠንክራ ማዕቀብ የሚጣልባት መሆኑን በመግለጽ ሲያስጠነቅቁ መቆየታቸው ይታወቃል፡፡