ባህር ዳር —
አማራ ክልል ውስጥ በተከሰተው የተፈጥሮና ሰው ሰራሽ አደጋዎች ምክንያት ከሦስት ሚልየን በላይ ሰው የእለት ምግብ እንደሚያስፈልገው የክልሉ አደጋ መከላከልና ምግብ የዋስትና ማስተባበሪያ ፕሮግራምና ልዩ ድጋፍ የሚሹ አካባቢዎች ኮሚሽን አስታውቋል።
ድጋፍ የሚያስፈልጋቸው ወታደራዊ እንቅስቃሴዎች በተካሄዱባቸው የትግራይ አዋሳኝ አካባቢዎች የሚኖሩ፣ ከቤንሻንጉል እና ከኦሮሚያ የተፈናቀሉ፣ እንዲሁም በተፈጥሮ አደጋዎች ምክንያት ችግር ላይ የወደቁ ዜጎች መሆናቸውን ኮሚሽኑ ገልጿል።
በእርዳታ አሰጣጡ ላይ አሉ የተባሉ ችግሮችን ለማስወገድ የአስቸኳይ ጊዜ ምላሽ ማስተባበሪያ ማዕከል ቻግኒ ላይ መቋቋሙን ኮሚሽኑ አስታውቆ በመሆኑም እርዳታ ማድረስ የሚፈልጉ ድርጅቶችና ግለሰቦች ወደ ማዕከሉ ገቢ እንዲያደርጉ አሳስቧል።
ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።
Your browser doesn’t support HTML5