የዋግ ኽምራ ዞን 18 ቀበሌዎቹ ከታጣቂዎች ቁጥጥር ነፃ ባለመኾናቸው ለመልሶ ማቋቋሙ ጫና እንደፈጠረበት ገለጸ

Your browser doesn’t support HTML5

የዋግ ኽምራ ዞን 18 ቀበሌዎቹ ከታጣቂዎች ቁጥጥር ነፃ ባለመኾናቸው ለመልሶ ማቋቋሙ ጫና እንደፈጠረበት ገለጸ

በዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን፣ በአበርገሌ እና በጻግብጅ ወረዳዎች የሚገኙ 18 ቀበሌዎች፣ እስከ አሁን ከታጣቂዎች ነፃ አለመውጣታቸው፣ በመልሶ ማቋቋም እንቅስቃሴው ላይ አሉታዊ ተጽእኖ እንደፈጠረበት ገለጸ፡፡

የዞኑ መንግሥት ኮሙኒኬሽን መምሪያ እንደሚለው፣ በርካታ ሰዎች ተፈናቅለው ከነበሩበት ከሰቆጣ እና በዙሪያው ከሚገኙ መጠለያ ጣቢያዎች፣ ወደ ወረዳቸው እንዲመለሱ ቢደረግም፣ ራሱን የአገው ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ እያለ የሚጠራው ታጣቂ ቡድን አባላት፣ በተለያዩ ቀበሌዎች ውስጥ እየተንቀሳቀሱ በመኾናቸው፣ ወደ ወረዳው የመጣው ተፈናቃይ፣ ወደ ቀዬው ለመመለስ መቸገሩን አስታውቋል፡፡

የአገው ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ የውጭ ግንኙነት ሓላፊ፣ ታጣቂዎቻቸውም ከአካባቢያቸው ወደ ሌላ ቦታ ሊሔዱ እንደማይችሉ ጠቁመው፣ የታጣቂዎቻቸው መኖር ግን፣ የመንግሥትን እንቅስቃሴ እንደማያስተጓጉል አስረድተዋል፡፡

ሙሉ ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።