የአፍሪካ ኅብረት ታዛቢዎች ይሠማራሉ

የምሥራቅ አፍሪካ ተጠባባቂ ኃይል 6ኛውን ጠቅላላ ምርጫ የሚታዘቡ 28 ታዛቢዎችን ወደ ተለያዩ የኢትዮጵያ አካባቢዎች እንደሚያሠማራ ገለፀ።

የተጠባባቂ ኃይሉ የምርጫ ታዛቢ ተልዕኮ ኃላፊ አምባሳደር አብዱላሂ ምርጫው የሚካሔደው በፈታኝ ወቅት መሆኑን ጠቁመው “የተቋሙ ዓላማ በአባል ሀገሮች ውስጥ የተረጋጋ ሁኔታ እንዲኖር ለማስቻል ተዓማኒ ምርጫ እንዲካሔድ ማገዝ ነው” ብለዋል፡፡

ለቪኦኤ አስተያየታቸውን የሰጡት የታዛቢ ቡድኑ መሪ በኢትዮጵያ ስለሚካሔደው ምርጫ እስካሁን ባገኙት መረጃ መሠረት ምርጫው ሰላማዊ ሆኖ እንደሚጠናቀቅ ያላቸውን እምነት ገልፀዋል፡፡

ለዝርዝሩ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

Your browser doesn’t support HTML5

የአፍሪካ ኅብረት ታዛቢዎች ይሠማራሉ