በአፍጋኒስታን በገበያ ሥፍራ በደረሰ ጥቃት በርካቶች ተገደሉ

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት

በአፍጋኗ ምስራቃዊ ናንጋርሃር ክፍለ ግዛት በገበያ ሥፍራ በተፈጸመ ጥቃት “በርካታ” ሰዎች ሲገደሉ፤ ሌሎች በርካቶች መቁሰላቸውን ሮይተርስ የዜና ወኪልን ዋቢ በማድረግ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የአፍጋኒስታን ተልዕኮ ዛሬ አስታወቀ።

በአፍጋኒስታን የሚገኘው የመንግሥታቱ ድርጅት ዕርዳታ ሰጪ ተልእኮ በትዊተር ገፁ ላይ እንዳሰፈረው ከተገደሉት እና ከቆሰሉት መካከል ህጻናት መኖራቸውንም አመልክቷል።

ይሁንና ታሊባን በበኩሉ ያረጋገጠው 10 ብቻ መቁሰላቸውን መሆኑን የሮይተርስ ዘገባ አመልክቷል።

መግለጫው “እየቀጠለ ያለው” ያለው "በአፍጋኒስታን በሲቪሎች የተነጣጠረ ጥቃት በአስቸኳይ መቆም አለበት" ሲል አሳስቧል።

ለጥቃቱ እስካሁን ኃላፊነት የወሰደ ማንም የለም።