አሜሪካ ለዩክሬን የምትሰጠውን ወታደራዊ ርዳታ አቋረጠች

  • ቪኦኤ ዜና

Your browser doesn’t support HTML5

አሜሪካ ለዩክሬን የምትሰጠውን ወታደራዊ ርዳታ አቋረጠች

አውሮፓ በዩክሬን ያለውን ጦርነት ለማስቆም የሚደረገውን ጥረት ለመምራት በመጣደፍ ላይ ስትሆን፣ የአሜሪካው ፕሬዝደንት በበኩላቸው ለዩክሬን የሚሰጠውን ማንኛውንም ወታደራዊ ርዳታ ትላንት ሰኞ እንዲቋረጥ አድርገዋል። ርምጃው የመጣው ትረምፕና ቮሎዲሚር ዜለንስኪ ባለፈው ዐርብ በዋይት ሐውስ ውይይት ባደረጉበት ወቅት፣ ትረምፕ ዜለንስኪን ጠንከር አድርገው መወረፋቸውን ተከትሎ ነው። መላው ዓለምም በዩክሬን ባለው ግጭትና በዋይት ሃውስ በተከሰተው ጉዳይ ላይ ትኩረቱን አድርጎ ነበር።

የቪኦኤ የዋይት ሐውስ ዘጋቢ አኒታ ፓወል ያጠናቀረችውን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።