‘ዩናይትድ ስቴትስ በውጭ ፖሊሲዋ የተነሳ ይበልጥ ጠንካራ ነች’ - ባይደን

  • ቪኦኤ ዜና

ፎቶ ፋይል፦ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን

ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ከስልጣን ጊዜያቸው ማብቂያ አንድ ሳምንት አስቀድሞ ትላንት ሰኞ ባሰሙት ንግግር የተመሩበትን የውጭ ፖሊሲ መርህ ዘርዝረዋል።

Your browser doesn’t support HTML5

‘ዩናይትድ ስቴትስ በውጭ ፖሊሲዋ የተነሳ ይበልጥ ጠንካራ ነች’ - ባይደን

አገሪቱን ወደ ፍጹም አዲስ ወደ ሆነ አቅጣጫ እንደሚመሩ በመግለጽ የዛቱት ተመራጩ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የመንግስቱን ሥልጣን ሊረከቡ የቀናት እድሜ ብቻ በቀረበት ሰዓት ባይደን ባሰሙት በዚህ ንግግራቸው፤ ዩናይትድ ስቴትስ ለምን በያዘችው መንገድ መቀጠል እንዳለባት መከራከሪያ አቅርበዋል።

የአሜሪካ ድምጿ ዘጋቢ አኒታ ፓውል ከኋይት ሃውስ ያጠናቀረችውን ዘገባ ዝርዝር አሉላ ከበደ እንደሚከተለው ያቀርበዋል።