የሩስያ መከላከያ ሚኒስቴር የሀገሪቱ ጦር በዩክሬን ምሥራቃዊ ሉሃንስክ ግዛት ውስጥ የምትገኘውን ናዲያ የተባለችውን መንደር መቆጣጠሩን እና በዩናይትድ ስቴትስ የተሠሩ ስምንት የአርሚ ታክቲካል ሚሳኤል ሲስተም (ATACMS) ሚሳኤሎችን መምታቱን ሮይተርስ ዘገበ።
የጦር ሜዳውን ውሎ መረጃዎች ግን ማረጋገጥ እንዳልቻለ በዘገባው ጠቅሷል።
ሚኒስቴሩ ፣ የሀገሪቱ የአየር መከላከያ ስርዓት ቅዳሜ ማለዳ በሰሜናዊ ሌኒንግራድ አካባቢ የተመቱትን ሦስቱን ጨምሮ ፣ በሩሲያ አየር ክልል ውስጥ የገቡ ዐሥር የዩክሬን ሰው አልባ አውሮፕላኖችን መትቶ መጣሉን አክሏል።
በሴንት ፒተርስበርግ የሚገኘው ፑልኮቮ አየር ማረፊያ ቅዳሜ ማለዳ ላይ ማናቸውም በረራዎችን ለጊዜው አቁሟል።