በትግራይ ክልል የወርቅ ማዕድን ሥራ ተቋርጦ ጥናት እንዲደርግ የክልሉ ጊዚያዊ አስተዳደር ካቢኔ መወሰኑን፣ የአስተዳደሩ ምክትል ፕሬዝዳንት ሌተናንት ጀነራል ጻድቃን ገብረተንሳኤ ገለጹ።
Your browser doesn’t support HTML5
ምክትል ፕሬዝዳንቱ፣ ትላንት እሁድ ከሽሬ እንዳስላሴ ተወላጆች ጋራ መቐለ ከተማ ላይ በአካሄዱት ውይይት፣ ከአምስት ወራት በፊት ተመሳሳይ ውሳኔ መወሰኑን አስታውሰው፣ “መንግሥት ውሳኔውን ለማስፈፀም ተቸግሯል” ብለዋል።
በሌላ በኩል፣ በትግራይ ሰሜናዊ ምዕራብ ዞን የወርቅ ማዕድን ቁፏሮ ጉዳይ ዘገባ በመሥራት ላይ የነበሩ የመንግሥታዊው ትግራይ ቴሌቭዥን ዘጋቢ ቡድን አባላት ትላንት ከሰዓታት እስር በኋላ መለቀቃቸው ታውቋል።
/ሙሉ ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ያዳምጡ/