የሶማሊያ እና ብሩንዲ ውዝግብ በአዲሱ የሰላም ተልዕኮ ሽግግር ላይ ስጋት ደቅኗል

በሶማሊያ የቡሩንዲ የአፍሪካ ህብረት ሰላም አስከባሪ ሃይል


በሶማሊያ የሚሰማሩ የብሩንዲ ወታደሮች ቁጥርን በተመለከተ በሶማሊያ እና ብሩንዲ ሀገራት መካከል የተፈጠረው አለመግባባት ወደ አፍሪካ ህብረት የሰላም ተልዕኮ ማምራቱን ተከትሎ በሰላም ተልዕኮው ሽግግር ላይ ስጋት ደቅኗል ።

ሶማሊያ በተልዕኮው ውስጥ 1041 የብሩንዲ ወታደሮች እንዲሳተፉ የደለደለች ቢሆንም ብሩንዲ ግን ቁጥር በቂ ያልሆነ እና የወታደሮቿን ድጋፍ እና ስምሪት ደህንነት ለአደጋ የሚያጋልጥ መሆኑን ተናግራለች። ብሩንዲ በትንሹ 2000 ወታደሮችን ለማሰማራት እንደምትሻ ዲፕሎማቶች ተናግረዋል።

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የጸጥታው ምክር ቤት ፣ አዲስ ለተቋቋመውን የአፍሪካ ህብረት ፣ የሶማሊያ ድጋፍ እና መረጋጋት ተልዕኮ (ኤዩሶም) ድጋፍ ሰጥቷል ።ተልዕኮው በስራ ላይ የቆየውን የአፍሪካ ህብረት የሽግግር ተልዕኮ በሶማሊያ (አትሚስ) ከአውሮፓዊያኑ ጥር 1.2025 ጀምሮ ይተካል ።አዲሱ ተልዕኮ በሀገሪቱ ውስጥ ለ12 ወራት ይሰማራ ዘንድ ጸድቆለታል።


የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ፣ የአፍሪካ ህብረት 1,040 ፖሊሶችን ጨምሮ እስከ 12,626 መለዮ ለባሾችን እስከ ሰኔ 30 ፥ 2025 በሚዘልቀው የተልዕኮው የመጀመሪያ ምዕራፍ የስራ ዘመን እንዲያሰማራ ስልጣን ሰጥቶቷል።የሶማሊያ ባለስልጣናት እስካሁን ድረስ ከሶስት ሀገራት -ማለትም ከዮጋንዳ ፣ ጅቡቲ እና ኬንያ 11000 ወታደሮችን ማካተታቸውን አስታውቀዋል።


በአውሮፓዊያን ታህሳስ 26 በሶማሊያ መከላከያ ሚኒስትር አብዱልቃድር ሞሐመድ ኑር የተጻፈው ደብዳቤ ፣የሚሰማሩ ብሩንዲ ወታደሮችን ቁጥር በተመለከተ ስምምነት ላይ አለመደረሱን ጠቁሟል ።

አንድ የብሩንዲ ዲፕሎማት ፣ የወታደሮችን ቁጥር በተመለከተ ልዩነት መኖሩን አረጋግጠዋል።

“የሶማሊያ ባለስልጣናት ወታደሮቻችንን ለአደጋ የሚያጋልጥ ቁጥር በመመደብ ክብራችንን ዝቅ አድርገዋል።ውለታን በመዘንጋት ፣ብሩንዲያውያን ለሶማሊያውያን ያላቸውን ጥልቅ ስሜት በቅጡ መገንዘብ አልቻሉም "፣ ሲሉ አንድ የብሩንዲ ባለስልጣን ለቪኦኤ አፍሪቃ ቀንድ አገልግሎት በዋትሳፕ መገናኛ በኩል መልዕክት ሰደዋል።

“በዛሬ እና በታህሳስ 31(እ ኤ አ) መካከል አንዳች ለውጥ ካልተፈጠረ ወደ ሀገራችን እንመለሳለን ።ለመቆየት አንጓጓም ። ክብራችን ተነክቷል ፣ ስለሆነም ይቅርታን እንሻለን " ሲሉም ዲፕሎማቱ አክለዋል ።

ለወታደሮች ቅነሳ ብሎም በታህሳስ 2024 ሶማሊያን ለቆ ለመውጣት የሚያስችል የጊዜ ተመን ለመበየን የሚያስችል የስራ መዋቅር ተፈጻሚ ከሆነ በኃላ የቀድሞው የሶማሊያ የሰላም ተልዕኮ በምሕጻሩ "አሚሶም" ከአውሮፓዊያኑ 2022 በኃላ በ አትሚስ ተተክቷል።

የወታደሮቹ የመልቀቂያ ጊዜ እየተቀራበ በመጣበት በአሁኑ ጊዜ ፣ የአፍሪካ ህብረት ፣ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ፣ እና የሶማሊያ መንግስት -አልሸባብ አሁንም አደጋ በመጣል ፣ የተገኙ ድሎችን እንዳይቀለብስ ስጋት አድሮባቸዋል። በዚህም ምክንያት የሶማሊያ መንግስት ወታደሮቹን ለማዘጋጀት ተጨማሪ ጊዜ የሚሰጠውን አዲሱን የአፍሪካ ህብረት ፣ የሶማሊያ ድጋፍ እና መረጋጋት ተልዕኮ (ኤዩሶም) ማቋቋም አስፈልጓል።

ከዚህ በተጨማሪ በአዲሱ የአፍሪካ ህብረት ተልዕኮ ውስጥ ኢትዮጵያ የሚኖራት ሚናም አለየም ። የኢትዮጵያ ባለስልጣናት በተልዕኮው ውስጥ ለመሳተፍ ዝግጁ መሆናቸውን ቢናገሩም ፣ አንዳንድ ባለስልጣናት ግን የኢትዮጵያን ሚና ይጠራጠሩታል።