የቀድሞው የእግር ኳስ ተጫዋች የጆርጂያ ፕሬዚደንት ሆኖ መመረጥ ለአውሮፓ ህብረት ዓላሚዎች ጉዳት ሆኗል

የ53 አመቱ ካቬላሽቪሊ  ፣2017ቱን ቀጥተኛ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ በተካው ሰርዓት መሰረት ለጆርጂያ ህልም ፓርቲ  የተሰጡ  300 የመራጭ ወኪል መቀመጫዎችን  በመቆጣጠር በቀላል ድምጽ አሸንፈዋል።

የቀድሞው የእግር ኳስ ተጫዋች ሚኬይል ካቬላሽቪሊ የጆርጂያ ፕሬዝደንት ሆነው መመረጣቸው በዛሬው ዕለት ይፋ ተደርጓል ።ዜናው የተሰማው ተቃዋሚዎች ሀገሪቱ የአውሮፓ ህብረትን ለመቀላቀል ያላትን ፍላጎት መና የሚያስቀር ፣ ለቀድሞዋ የሀገሪቱ ንጉሳዊ አስተዳደር ገዢ ሩሲያ ድል የሚያቀናጅ ሲሉ የጠሩት የገዥው ፓርቲ እርምጃ እየበረታ በመጣበት ወቅት ነው።

የ53 አመቱ ካቬላሽቪሊ ፣2017ቱን ቀጥተኛ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ በተካው ሰርዓት መሰረት ለጆርጂያ ህልም ፓርቲ የተሰጡ 300 የመራጭ ወኪል መቀመጫዎችን በመቆጣጠር በቀላሉ አሸንፈዋል።

በደቡባዊ ካውካሷ ሀገር ፣ የጆርጂያ ህልም ፓርቲ ጥቅት 26 በተደረገው ምርጫ ፓርላማውን መቆጣጠር የቻለው በሞስኮ ድጋፍ ምርጫውን በማጭበርበር ነው ሲሉ ተቃዋሚዎች ይከሳሉ።

የጆርጂያ ተሰናባች ፕሬዝዳንት እና ዋና ዋና አፍቃሪ ምዕራብ ፓርቲዎች ፣ በፓርላማ ስብሰባዎች ላይ አድማ በመምታት ዳግመኛ ምርጫ እንዲካሄድ ጥሪ አቀርበዋል።

የጆርጂያ ህልም ፓርቲ የአውሮፓ ህብረትን ለመቀላቀል ግፊት እንደሚያደርግ ፣ አብሮም ከሩሲያ ጋር ያለውን ግንኙነት እንደሚያድስ ቃል ገብቷል።

በአውሮፓዊያኑ 2008 ሩሲያ ከጆርጂያ ጋር አጭር ጦርነት ውስጥ ገብታ የነበረ ሲሆን ፣ ይህም ሞስኮ ሁለት ተገንጣይ ክልሎችን እንደ ገለልተኛ ሀገራት እውቅና እንድተሰጣቸው መርቷታል። በደቡብ ኦሴቲያ እና በአብካዚያ የሩሲያ ጦር ኃይል ስምሪት እንዲጨምርም አድርጓል ።

ባይደዚና አይቫንሽቪሊ በተባለ ፣ ሩሲያ ውስጥ ሀብቱን ባፈራ ቢሊየነር ፣ የተመሰረተው የጆርጂያ ህልም ፓርቲ ከቀን ተቀን አምባገነን እየሆነና እና ወደ ሩሲያ እያጋዳለ ስለመሆኑ ትችት ይቀርብበታል ።ገዥው ፓርቲ ግን ክሱን አይቀበልም ።

ፓርቲው በቅርቡ ክሬምሊን የመናገር ነፃነትን እና የኤልጂቢቲኪው+ መብቶችን ለመግታት የሚጠቀምባቸውን ዓይነት ህጎችን አውጥቷል።

አፍቃሪ ምዕራብ የሆኑት ሰሎሜ ዙራቢችቪሊ ከ2018 ጀምሮ የሀገሪቱ ፕሬዚደንት ሆነው ያገለገሉ ሲሆን ፣ የስድስት አመት የስልጣን ዘመናቸው ሰኞ ዕለት ያበቃል ። እራሳቸውን ብቸኛ ህጋዊ መሪ ሲሉ የሚገልጹት ፕሬዚደንቷ አዲስ ምርጫ እስኪደረግ ድረስ በስልጣናቸው እንደሚቆዩ ተናግረዋል።

የጆርጂያ ህልም ባለፈው ወር ፣ ሀገሪቱ ወደ አውሮፓ ህብረት ለመቀላቀል የምታደርገውን ድርድር ለማቆም መወሰኑ የተቃዋሚዎችን ቁጣና ተቃውሞ አባብሶታል።

የእንግሊዙ ማንቺስተር ሲቲ ክለብ እና በስዊዝ ሱፐር ሊግ ውስጥ በሚገኙ ክለቦች የቀድሞ ተጫዎች የነበሩት ፣ለፕሬዚደንትነት በጆርጂያ ህልም ፓርቲ የተመረጡት ካቪላሽቪሊ ባላቸው ዝቅተኛ ትምህርት ደረጃ ተቃዋሚዎች ሲሳለቁባቸው ቆይተዋል ።
በ2016 የአውሮፓዊያኑ ዘመን በጆርጂያ ህልምን ፓርቲ በመወከል የፓርላማ ተመራጭ ከሆኑ በኃላ የህዝቦች
ኃይል ፖለቲካዊ ንቅናቄ የተሰኘ ፓርቲ በአውሮፓዊያኑ 2022 መስርተዋል። ይህ ፓርቲ የጆርጂያ ህልም ፓርቲ አጋር ሲሆን በጠንካራ ጸረ ምዕራባዊያን አቋሙ ይበልጡኑ ዕውቅና አግኝቷል።