የትግራይ ክልል በአሰቃቂው ጦርነት እና ረሃብ ከደረሰበት ጉዳት ለማገገም እየታገለ ባለበት በአኹኑ ወቅት፣ ለሃብት ዝርፊያ መጋለጡን እና የወርቅ ማዕድን ለማውጣት ጥቅም ላይ ለሚውሉ አደገኛ ኬሚካሎች የመጋለጥ ዕጣ የተጋረጠበት መሆኑን ነዋሪዎች እና ባለሥልጣናት ተናገሩ።
በማዕድን ማውጫው አቅራቢያ የሚኖሩ ነዋሪዎች ኬሚካሉ በሰውና በእንስሳት ላይ ጉዳት እያደረሰ መሆኑን የገለጹ ሲሆን፤ ኬሚካሉ የላሞችን ቆዳ እያበላሸ እና መሬት እያራቆተ መሆኑን የዐይን እማኞችና ባለስልጣናቱ ተናግረዋል።