መስከረም አበራ የአንድ ዓመት ከ4 ወር እስር ተፈረደባት

ፎቶ ፋይል፦ “ኢትዮ ንቃት” የተሰኘ የዩቲዩብ ብዙኃን መገናኛ አዘጋጅ መስከረም አበራ

Your browser doesn’t support HTML5

መስከረም አበራ የአንድ ዓመት ከ4 ወር እስር ተፈረደባት

የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዛሬ በዋለው ችሎት በመስከረም አበራ ላይ የ1 ዓመት ከ4 ወር እስር መፍረዱን ጠበቃዋ ለአሜሪካ ድምፅ ገልጸዋል፡፡

“በኮምፒውተር ተጠቅማ በኅብረተሰብ መካከል አመጽ፣ ሁከት እና ግጭት ለማነሳሳት ሞክራለች” በሚል ጥፋተኛ በተባለችባቸው ሁለት ወንጀሎች እንደተፈረደባት ጠበቃዋ ተናግረዋል።

ዛሬ የቅጣት ውሳኔው ከተሰጠበት የክስ መዝገብ ሌላ፣ በአማራ ክልል ካለው የፀጥታ መደፍረስ ጋራ በተገናኘ ደግሞ በእነ ዶ/ር ወንድወሰን አሰፋ መዝገብ ስር ከሌሎች 50 ተከሳሾች ጋራ የሽብር ክስ የተመሰረተባት መስከረም አበራ፣ ከሚያዝያ 1 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ በእስር ላይ ትገኛለች፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ፡፡