ባይደን እና ትራምፕ በዋይት ኃውስ ተገናኙ

  • ቪኦኤ ዜና

Your browser doesn’t support HTML5

ትራምፕ እና ባይደን በዋይት ኃውስ ተገናኙ

ባለፈው ሳምንት ምርጫውን ካሸነፉ ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ ዛሬ ወደ ዋሽንግተን የተመለሱት የቀድሞው ፕሬዝደንት ዶናልድ ትረምፕ፣ ከፕሬዝደንት ጆ ባይደን ጋራ ዋይት ኃውስ ውስጥ ተገናኝተው እጅ ለእጅ ተጨባብጠዋል።

ጆ ባይደን ትረምፕን ወደ ዋይት ኃውስ የጋበዟቸው ሰላማዊ የሥልጣን ሽግግር ለማድረግ ሲሆን በዛም እንደደረሱ “ዶናልድ እንኳን ደስ አለህ” ብለዋቸዋል።

"መጪው ፕሬዝዳንት እና የቀድሞ ፕሬዝዳንት ዶናልድ፣ እንኳን ደስ አልዎት። እንዳልነው በቀጣይ ሰላማዊ ሽግግር ለማድረግ በጉጉት እየጠበቅን ነው። የሚፈልጉትን ለማድረግ የምንችለውን እያደረግን ነው፣ እናም የተወሰነውን አሁን ለመነጋገር እድል እናገኛለን።"

ትራምፕ በበኩላቸው ባይደን ላደረጉላቸው አቀባበል አመስግነው፣ "በአንዳንድ ነገሮች የፖለቲካው ዓለም አስደሳች አይደለም። ዛሬ ግን አስደሳች ነው። ሰላማዊ የሆነ የስልጣን ሽግግር መደርጉን አደንቃለሁ። ከዚህ በዋላ በሚቻለው ሁሉ የተረጋጋ ሽግግር ይሆናል። በጣም ደስ የሚያሰኝ ነው። አመሰግናለሁ" ሲሉ ፖለቲካ አስቸጋሪ መሆኑን ግን ደግሞ በተደረገላቸው መደሰታቸውን ገልጸዋል።

ትራምፕ ዛሬ ጠዋት አውሮፕላናቸው ሜሪላንድ በሚገኘው ጆይንት ቤዝ አንድሩስ የአየር ኃይል ወታደራዊ ቅጥር ያረፈ ሲሆን፣ በካፒቶል የሚገኙ የሪፐብሊካን አባላትንም አግኝተው ንግግር አድርገዋል።

ትረምፕ ከአራት ዓመታት በፊት በምርጫው በተረቱበት ወቅት ባይደንን ወደ ዋይት ሃውስ አልጋበዙም። በባይደን በዓለ ሹመት ላይም አልተገኙም።