ትረምፕ መመረጣቸውን ተከትሎ የቢትኮይን ዋጋ አሻቅቧል 

በዩናይትድ ስቴትስ ዶናልድ ትረምፕ በፕሬዚደንታዊ ምርጫው ማሸነፋቸውን ተከትሎ አስተዳደራቸው ለኢንተርኔት መገበያያው አመቺ ሁኔታ ያመጣል በሚል በፈጠረው ከፍተኛ ተስፋ ዛሬ የቢትኮይን ዋጋ ወደዘጠና ሺህ ገደማ ማሻቀቡ ተገለጸ።

ከዓለም ትልቁ ክሪፕቶ ወይም በኢንተርኔት ላይ መገበያያ ገንዘብ ቢትኮይን ከአሜሪካ ምርጫ ወዲህ በቀጠሉት ቀናት በዓለም ግብይት ትልቅ ትኩረት ከሳቡት መካከል ሲሆን ከምርጫው ወዲህ ዋጋው ከ30 ከመቶ በላይ አድጎ በ89 ሺህ 982 ዶላር ተሽጧል።

የኢላን መስክ የኦቶሞቢል ኩባኒያ ቴስላ ዋጋም በ40 ከመቶ ገደማ ማደጉን የሮይተርስ ዘገባ አመልክቷል።