ትረምፕ " የአየር ንብረት ለውጥን  ለመቆጣጠር በታለሙ ፖሊሲዎች ላይ አነጣጥረዋል" ተባለ 

ዶናልድ ትረምፕ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንት ሆነው በድጋሚ መመረጣቸው ብሎም ሪፐብሊካኖች የህግ መወሰኛ ምክር ቤቱን መቆጣጠራቸው ብዙዎችን የሀገሪቱን የአየር ንብረት ፖሊሲዎች መሰረዝ ሊያስከትል እንደሚችል የአየር ንብረት ደህንነት አዋቂዎች ተናገሩ።

የከባቢ አየር ግለት የሚያስከትል ጋዝ ልቀትን ለመቀነስ ከሁሉም ውጤት ያስመዘገቡ ሲሉ የዘርፉ አዋቂዎች የዘረዘሯቸው ሥራዎች ትረምፕ እርምጃ እወስዳለሁ ብለው ያነጣጠሩባቸው ፖሊሲዎች መሆናቸውን የአሶስየትድ ፕሬስ ዘገባ አመልክቷል።

ዶናልድ ትረምፕ በአየር ንብረት ለውጥ ፖሊሲዎች ላይ እርምጃ የሚወስዱት በከባድ የሙቀት ማዕበል ብዙ ሰዎች ህይወት እየጠፋ ባለበት እና የከባቢ አየር ብክለት ከምንጊዜውም አስከፊ ደረጃ ላይ በደረሰበት በአሁኑ ወቅት መሆኑን ያከለው ዘገባው አያይዞም ዩናይትድ ስቴትስ እጅግ አውዳሚ በሆኑ ሁለት የባህር ማዕበል ወጀቦች (ኸሪኬይን) መመታቷን አስታውሷል።