ራሷን ነጻ ሀገር አድርጋ ያወጀቸው የሶማሊላንድ ሪፐብሊክ የፊታችን ረቡዕ ፕሬዝደንታዊ ምርጫ ታካሂዳለች፡፡
የዕጩ ተፎካካሪዎቹ የምርጫ ዘመቻም ትላንት እሁድ ተጠናቋል፡፡ ሦስቱ ተፎካካሪ ፓርቲዎች በምርጫው ዋዜማ እያንዳንዳቸው ለየብቻቸው አንድ ቀን ተሰጥቷቸው በመላ ሀገሪቱ ዘመቻቸውን አጠናቅቀዋል፡፡
በሶማሊላንድ የምርጫ አፈጻጸም ደንብ መሠረት ከምርጫው በፊት ባሉት ሁለት ቀናት በጎዳናዎች ላይ የምረጡኝ ቅስቀሳም ኾነ የድጋፍ ስብሰባ አይፈቀድም፡፡
ሀሩን ማሩፍ ከዋሽንግተን ያጠናቀረው ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።
Your browser doesn’t support HTML5