እስራኤል በማዕከላዊ ጋዛ ባደረሰችው ጥቃት 47 ሠሰዎች ሲገደሉ በደርዘን የሚሆኑ ደግሞ መቁሰላቸውን የፍልስጤም ዜና ወኪል (ዋፋ) አስታውቋል።
ሌሌት በተፈጸመው ድብደባ የተገደሉት አብዛኞቹ ሴቶችና ሕፃናት መሆናቸውንም ዜና አገልግሎቱ ጨምሮ አስታውቋል።
የእስራኤል ሠራዊት በበኩሉ በማእከላዊ ጋዛ “በርካታ የታጠቁ አሸባዎሪች” ብሎ የገለጻቸውን ለይቶ መደምሰሱን እንዲሁም በሰሜን ጋዛ ደግሞ በደርዘን የሚቆጠሩና ሽብርተኖች ያላቸውን መደምሰሱን አስታውቋል።
የእስራኤል ጥቃት ከ43 ሺሕ በላይ ፍልስጤማዉያንን መግደሉንና የጋዛ ሰርጥን ወደ ፍርስራሽ መቀየሩን የፍልስጤማውያን ባለስልጣናት አስታውቀዋል።
ዓለም አቀፍ አካላት በጋዛ ሰርጥ የሚገኙትን “ሆስፒታሎችና የጤና ሠራተኞች ከእስራኤል ጨካኝ አያያዝ ይከላከሉ” ሲል በጋዛ ሰርጥ የሚገኘው የጤና ሚኒስቴር ጥሪ አድርጓል። ድንበር የለሹ የሐኪሞች ቡድን (MSF) በበኩሉ በሆስፒታል ከሚሠሩት የቡድኑ ዶክተሮች ውስጥ አንዱ ባልለፈው ቅዳሜ በእስራኤል ኃይሎች ተይዞ መወሰዱን አስታውቋል።