Your browser doesn’t support HTML5
ካማላ ሃሪስ የዲሞክራት ፓርቲያቸው እጩ ሆነው መቅረባቸውን ተከትሎ፤ እስካሁን ሴት ፕሬዝዳንት መርጠው የማያውቁት አሜሪካውያን፤ ሴት ፕሬዚደንት መርጠው ‘በዓለም እጅግ ገናና ተደርጎ ለሚታየው የሥልጣን እርከን ለማብቃት ተዘጋጀተው ይሆን?’ የሚለው ጥያቄ ዳግም እያነጋገረ ነው።
በዋሽንግተን ዲሲ ብሩኪንግስ ዓለም አቀፍ ጥናት ተቋም የምጣኔ ሃብት እና የልማት ጉዳዮች አጥኚ ዶ/ር አዲሱ ላሽተው በጉዳዩ ላይ ማብራሪያ ሰጥተውናል።
ዶ/ር አዲሱ የምርጫው ሂደት የሚጠይቀው ሰፊ መሰረት ያለው አጋዥ ሁኔታ ወሳኝ መሆንም፤ ወንዶች ብቻ የመሪነቱን ሥልጣን ይዘው በቆዩበት የፖለቲካ ምኅዳር ለሴቶች ቀላል ያለመሆኑን ያስረዳሉ። ሴቶች በማኅበረሰብ ውስጥ ያላቸው የመሪነት ሚና ከፍ ካለ ደረጃ ቢደርስም፤ “አሁንም ገና ይቀረዋል” የሚሉት ዶ/ር አዲሱ “ካማላ ሃሪስ ከጾታቸው በተጨማሪ ጥቁር መሆናቸውም የራሱን ተጽእኖ ማሳደሩ እንደማይቀርም ያስረዳሉ። /ሙሉውን የተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።