ዩናይትድ ስቴትስ ለታይዋን ባጸደቀችው የ2 ቢሊዮን ዶላር የጦር መሳሪያ ሽያጭ ጥቅል ውስጥ በዩክሬን የተሞከረው የላቀ የአየር መከላከያ ሚሳኤል ጭምር መካተቱንና ለመጀመርያ ጊዜ ወደ ደሴቷ የሚላክ መሆኑን ፔንታጎን ትላንት አርብ አስታውቋል፡፡
ዩናይትድ ስቴትስ በቻይና ይገባኛል ጥያቄ ከምታነሳባት ታይዋን ጋር ምንም እንኳን መደበኛ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ባይኖራትም ራሷን እንድትከላከል የሚያስችል ድጋፍ ለመስጠት በህግ ትገደዳለች፤ ይህ ደግሞ የቤጂንግ የሁልጊዜ ቁጣ ነው።
ቻይና ያለፈውን ሳምንት ጨምሮ በታይዋን ላይ የምታካሄዳቸው ወታደራዊ ጫናዎች እየጨመረ ሲሆን ይህም በግንቦት ወር ላይ ቺንግ-ቴ የታይዋን ፕሬዝዳንት ሆነው ስልጣን ከያዙ በኋላ ለሁለተኛ ጊዜ ያካሄደችው ወታደራዊ እንቅስቃሴነው፡፡
የፔንታጎን የመከላከያ ደህንነት ትብብር ኤጀንሲ እንዳስታወቀው አዲሱ ሽያጭ 828 ሚሊዮን ዶላር የሚገመት ዋጋ ያላቸው 1.16 ቢሊዮን ዶላር የሚያወጡ የሚሳኤል እና ራዳር ስርዓት መሳርያዎችን ያካተተ ነው።
የታይዋን መከላከያ ሚኒስቴር መግለጫውን በደስታ እንደተቀበለው አስታውቋል፣ የአየር መከላከያዎቹ በቻይና የሚደረጉ ተደጋጋሚ ወታደራዊ እንቅስቃሴዎችን ለመከላከልና የታይዋን የአየር መከላከያ አቅም ለማሳደግ ያግዛል ብሏል፡፡
የታይዋን ጦር ከቻይና የሚደርስ ማንኛውንም ጥቃት በተሻለ ሁኔታ ለመቋቋም ወሳኝ የባህር ሃይል መከላከያ የራሱን ሰርጓጅ መርከብ መገንባትን ጨምሮ ትጥቁን እያጠናከረ ይገኛል።