Your browser doesn’t support HTML5
በኦሮሚያ ክልል፣ ምዕራብ ወለጋ ዞን በሚገኙ የተለያዩ ወረዳዎች ውስጥ፣ በመንግሥት ኃይሎች እና በኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት ታጣቂዎች መካከል በቀጠለው ግጭት፣ ሲቪሎች መገደላቸውን ነዋሪዎች ገለጹ። የመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች "ለታጣቂዎቹ ታገለግላላችኹ" ፣ ታጣቂዎቹ ደግሞ "ለመንግሥት ትሠራላችኹ" በሚል ከሁለቱም በኩል ጉዳት እየደረሰባቸው እንደኾነ፣ ለቪኦኤ አስተያየት የሰጡ ነዋሪዎች ተናግረዋል።
ጉዳቱ ደርሶበታል የተባለው፣ የቆንዳላ ወረዳ አስተዳዳር፣ ተገደሉ ስለተባሉ ሲቪሎች መረጃ እንደሌለው አስታውቋል። መንግሥት በሲቪሎች ላይ ጥቃት እንደማያደርስም የወረዳው አስተዳዳሪ ገልጸዋል። የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን በአካባቢው ይፈፀማል የተባለው ጥቃት ሪፖርት እንደደረሰው አስታውቋል።
/ዝርዝርሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ/