በአዲስ አበባ በመርካቶ ሸማ ተራ አከባቢ ዛሬ ማምሻውን እሳት መከሰቱ ታውቋል።
“በተከሰተው የእሳት አደጋ በንብረት ላይ ለደረሰው ጉዳት እጅግ አዝነናል” ያሉት የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ፣ “የተከሰተውን የእሳት አደጋ ለመቆጣጠር ከእሳት አደጋ እና ስጋት መከላከል እንዲሁም ከአካባቢው ማህበረሰብ ጋር በመሆን ርብርብ እየተደረገ” መሆኑን አመልክተዋል።
አደጋውን ለመቀነስ በመሥራት ላይ ያሉ አካላት ሁሉ ጥረታቸውን እንዲቀጥሉም ከንቲባዋ አሳስበዋል።
አደጋውን በአስቸኳይ ለመቆጣጠር አዳጋች የሆነው የአካባቢው መንገድ ለእሳት አደጋ መኪና እንቅስቃሴ አስቸጋሪ በመሆኑ ምክንያት መሆኑን የጠቆሙት ከንቲባዋ፣ በሄሊኮፕተር ለመጠቀም ጥረት በመደረግ ላይ መሆኑንም ገልፀዋል።