አፍሪካ በፀጥታው ምክር ቤት በሁለት ቋሚ አባል ሀገራት መወከል እንደሚገባት ጉተሬዥ ተናገሩ

Your browser doesn’t support HTML5

አፍሪካ በፀጥታው ምክር ቤት በሁለት ቋሚ አባል ሀገራት መወከል እንደሚገባት ጉተሬዥ ተናገሩ

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉተሬዥ አዲስ አበባ በሰጡት መግለጫ፣ በፀጥታው ምክር ቤት መሻሻል እና በአፍሪካ ውክልና ላይ በተመድ አባላት መካከል መግባባት መኖሩን ገልጸዋል።

ዓለም አቀፉ የገንዘብ ሥርዓትም አፍሪካን ተጠቃሚ በሚያደርግ መልኩ መሻሻል እንዳለበት ከስምምነት መደረሱን ዋና ጸሐፊው ጠቁመዋል፡፡

ዋና ጸሐፊው ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ጋራ በመሆን እድሳት የተደረገለትን የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን መቀመጫ የሆነውን የአፍሪካ አዳራሽም መርቀዋል፡፡