የኬኒያ ፕሬዚደንት የአገር አስተዳደር ሚኒስትሩን ምክትል ፕሬዚደንት አድርገው ሾሙ

  • ቪኦኤ ዜና

አዲሱ ምክትል ፕሬዚደንት ኪቱሬ ኪንዲኬን

ፕሬዚደንት ዊሊያም ሩቶ የሀገሪቱ ፓርላማ በሙስና እና የብሄረሰብ ግጭት በመቀስቀስ የከሰሳቸውን ምክትል ፕሬዚደንቱን ሪጋቲ ጋቻጉዋን በከፍተኛ ድምጽ ከሥልጣን ካባረራቸው በጥቂት ሰዓታት ተከትሎ የአገር አስተዳደር ሚኒስትሩን ኪቱሬ ኪንዲኬን አዲሱ ምክትል ፕሬዚደንታቸው አድርገው ለምክር ቤቱ አቅርበዋል።

የምክር ቤቱ አባላት በሙሉ ድምጽ ሹመቱን ያጸደቁ ቢሆንም ከፍተኛ ፍርድ ቤት ተተኪ የመሰየሙ ሂደት የጋቻጉዋን መባረር በመቃወም የቀረቡት አቤቱታዎች እስከሚታዩበት እስከ ቀጣዩ ሐሙስ ድረስ እንዲቋረጥ ትዕዛዝ ሰጥቷል።

የመባረራቸው ውሳኔ ሆስፒታል በተኙበት የተላለፈባቸው ጋቻጉዋ አሁንም ያልወጡ ሲሆን የህመማቸውን ሁኔታ ጠበቆቻቸው "ከጭንቀት ጋር የተያያዘ የደረት ላይ ህመም" ሲሉ ገልጸውታል።