Your browser doesn’t support HTML5
“በአዲስ አበባ ከተማ ከዛሬ ጀምሮ ተግባራዊ የተደረገው፣ አዲሱ የትራንስፖርት ክፍያ ጭማሪ፣ ኑሯችንን ያከብደዋል” ሲሉ ለአሜሪካ ድምፅ አስተያየት የሰጡ አንዳንድ የከተማዋ ነዋሪዎች ገለፁ፡፡
ስለ ጉዳዩ ለአሜሪካ ድምፅ ማብራሪያ የሰጡ አንድ የኢኮኖሚ ባለሙያ ደግሞ፣ የትራንስፖርት ክፍያን ጨምሮ፣ ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ እየጨመሩ ያሉት የአገልግሎት ክፍያዎች፣ በተለይም የታችኛውን የህብረተሰብ ክፍል ኑሮ እንደሚጎዱ ገልፀዋል፡፡ መንግስት፣ ኑሮን የሚያረጋጉ እና ጫናውን ለመቋቋም የሚያስችሉ እርምጃዎችን እንዲወስድም ባለሙያው ጠይቀዋል፡፡
ከአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ ምላሽና አስተያየት ለማግኘት ያደረግነው ጥረት ለዛሬ አልተሳካም፡፡