የአፍሪካ መከላከያ ሚኒስትሮች በአዲስ አበባ ስለአህጉሪቱ ሰላምና ፀጥታ በመወያየት ላይ ናቸው፡፡
ለአህጉሪቱ የመከላከያ ሚኒስትሮች የመጀመሪያ መሆኑ የተነገረውን ይህን ስብሰባ ኢትዮጵያ እንዳዘጋጀች ተገልጿል፡፡
የኢትዮጵያ መከላከያ ሚኒስትር ኢንጂነር አይሻ መሐመድ አፍሪካ በውስብስብ የፀጥታ ችግር ዉስጥ መሆኗን ተናግረዋል።
የስብሰባው ተሳታፊዎች በተለይ የአፍሪካ ተጠባባቂ ሠራዊት ኃይል ትግበራ ወደ ኋላ መጎተት፣ አገራት “በአህጉሪቱ ለሚያጋጥሙ ችግሮች ወደ ውጭ እንዲመለከቱ አድርጓል” ይላሉ፡፡