Your browser doesn’t support HTML5
በኦሮሚያ ክልል ፣ሰሜን ሸዋ ዞን፣ደራ ወረዳ፣በመንግሥት ኃይሎችና በኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት እንደዚሁም በመንግሥት ኃይሎችና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል ከመስከረም 27 ቀን 2017 ዓ/ም በቀጠለው ግጭት ሰባት ሰላማዊ ሰዎች ተገድለዋል ሲሉ የአካባቢው ነዋሪዎች ገልፀዋል።
ለደህንነታቸው በመስጋት ስማቸው እንዳይጠቀስ የጠየቁት እነዚሁ ነዋሪዎች እንዳሉት የሟቾቹ አስከሬን የተገኘው ጥቅምት 2 ቀን 2017 ዓ/ም. ነው።
የአሜሪካ ድምፅ ስለጉዳዩ ካነጋገራቸው ሁለት የዞንና የወረዳ ባለስልጣናት አንዱ “ምንም ውጊያ የለም” በማለት ሲያስተባብሉ፣ ሌላው በበኩላቸው ወረዳው “ከፀጥታ ችግር ውጭ ሆኖ አያውቅም” ብለዋል።