ቻይና የቬትናምን ድንበር ዘለል የባቡር ፕሮጀክቶችን ለማገዝ እና ወደ ሀገሯ የምታስገባውን የቬትናም የግብርና ምርቶችን ለመጨመር ተስማማታለች ሲሉ የቬትናም መገናኛ ብዙሃን ዛሬ እሁድ ዘግበዋል፡፡
ቬትናምን የጎበኙት የቻይናው ጠቅላይ ሚኒስትር ሊ ኪያንግ የቻይናን ገበያ ለቪዬትናም ፍራፍሬዎች ፣ የባህር ምግቦች እና ሌሎች ከፍተኛ ጥራት ያላቸውን ምርቶች ክፍት ለማድረግ ቃል ገብተዋል ።
ቻይና ከዩናይትድ ስቴትስ ለጥቃ የቬትናም ትልቁ የንግድ አጋር ስትሆን በመካከላቸው ያለው የሁለትዮሽ ንግድ እኤአ በ2023፣ 172 ቢሊዮን ዶላር ደርሷል።
ቻይናና ቬትናም 10 የትብብር ስምምነቶችን በመፈራረም በዲፕሎማሲ ፣ በብሔራዊ መከላከያ እና በሕዝብ ደህንነት ትብብርን ለማስፋት ተስማምተዋል ።
የቻይናው ጠቅላይ ሚኒስትር ወደ ቬትናም የመጡት በአገሯባቿ ላኦስ ከተካሄደው የደቡብ እስያ መሪዎች ስብሰባ በኋላ ነው፡፡ ስብሰባው በደቡብ ቻይና ባህር ያለውን የባህር ወሰን ውዝግብ ለመፍታት አለም አቀፍ የግዛት ህግ እንዲከበር ላቀረበው ጥሪ ምላሽ ሰጥተዋል፡፡
የቬትናም ጠቅላይ ሚኒስትር ፋም ሚን ቺንህ በተለይ የአሳ አጥማጆችን እና ጀልባዎቻቸውን እንቅስቃሴ አስመልክቶ ያለውን የባህር ላይ ውዝግብ በሰላማዊ መንገድ እንዲፈቱ አሳስበዋል፡፡
በዚሁ ስብሰባ የተገኙት የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንተኒ ብሊንከን ቻይና በደቡብ ቻይና ባህር ላይ የምታሳየውን እንቅስቃሴ ነቅፈዋል፡፡