ዩክሬን እና ሩሲያ እያንዳንዳቸው በደርዘን የሚቆጠሩ የድሮን ጥቃቶችን አከሸፍን እያሉ ነው

ዘለንስኪ ከጀርመኑ አቻቸው ኦላፍ ሹልዝ ጋር

ሩሲያ 46 የዩክሬን ድርኖችን መትታ መጣሏን ስትናገር በአንጻሩ ኪቭ 27 የሩሲያ ድሮኖችን መትቻለሁ አለች።

የዩክሬን አየር ሃይል ብዛታቸውን እና ዓይነታቸውን ሳይጠቅስ ከሩሲያ ድንበር ቤልጎሮድ ክልል አቅራቢያ ብዙ ሚሳኤሎች ተተኩሰዋል ሲል አስታውቋል።

ሩሲያ 28 ሰው አልባ አውሮፕላኖችን በዩክሬን ላይ ብትተኩስም ከእነዚህ ውስጥ 24ቱ በሱሚ፣ ፖልታቫ፣ ዲኒፕሮፔትሮቭስክ፣ ሚኮላዬቭ እና ኬርሰን ክልሎች ተመትተው ወድቀዋል ሲል መግለጫው አክሏል።

በተጨማሪም የዩክሬን ዋና የጦር አዛዥ ምንም እንኳን ዝርዝሩን ባይገልጹም የኪየቭ ሃይሎች በምሥራቃዊ ሩሲያ በተያዘችው ሉጋንስክ ክልል የሚገኝ የነዳጅ ማከማቻ መጋዘን መትተው በእሳት አቃጥለዋል ብለዋል።

ይሁን እንጂ ሞስኮ ጥቃቱን አላረጋገጠችም። ነገር ግን የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር ጦር ሃይል ሩሲያ በአንድ ጀምበር 47 የዩክሬን ሰው አልባ አውሮፕላኖችን መጣሏን ገልጸዋል። ድሮኖቹ 17ቱ በደቡብ ምሥራቅ ክራስኖዶር ክልል፣ 16 በአዞቭ ባህር እና 12 በሉርስክ ድንበር ላይ መውደቃችውን የጦር ሃይሉ ጨምሮ ገልጿል።

ሩሲያ ዩክሬንን ከወረረበት ከጎርጎርሳዊያኑ የካቲት 2022 ወዲህ ሀገሪቱ እጅግ ከባድ የሆነባትን የክረምት ወራት እየተጋፈጠች ተገናለች። በዚህ ወቅትም የሩሲያ ሀይሎች በምሥራቃዊ ግንባር በኩል ግስጋሴዎችን በማድረግ የዩክሬንን የሃይል አውታር ላይ ዒላማ አድርገዋል።