"የሀገር አቀፍ ፈተናውን ውጤት ዓመቱን በሙሉ ልንነጋገርበት ይገባል" ዶ/ር ሀዋኒ ንጉሴ

Your browser doesn’t support HTML5

"የሀገር አቀፍ ፈተናውን ውጤት ዓመቱን በሙሉ ልንነጋገርበት ይገባል" ዶ/ር ሀዋኒ ንጉሴ

የዘንድሮውን የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ከወሰዱ 674 ሺህ 823 ተፈታኞች ውስጥ 5.4 ከመቶ ብቻ ማለፋቸው እጅግ በጣም እንዳስደነገጣቸው እና እንዳሳዘናቸው ተማሪዎች እና መምህራን ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል።

ሀሳባቸውን ካጋሩን ምሁራን መካከል በደቡብ ካሊፎኒያ ማሳቹሴት ግሎባል ዲፓርትመንት ዋና ስራስኪያጅ ዶ/ር ሃዋኒ ንጉሴ ጋር ከአሜሪካ ድምጽ ጋር ቆይታ አድርገዋል፡፡ ዶ/ር ሀዋኒ የሀገር አቀፍ ፈተናው ውጤት ዓመቱን ሙሉ ሊወያዩበት፣ ሊመክሩበት የሚገባ ይባስ ብሎም የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ሊታወጅለት ጭምር የሚገባው በሀገር እና በትውልድ ላይ የመጣ ተግዳሮት ነው ይላሉ።

ከአሜሪካ ድምጽ ጋር ቆይታ አድርገዋል። ያነጋገረቻቸው ኤደን ገረመው ናት።