የውጭ ምንዛሬ በገበያ ዋጋ እንዲወሰን የሚያደርገው የኢኮኖሚ ማሻሽያ በአይ ኤም ኤፍ አስግዳጅነት የተተገበረ ሳይሆን፤ መንግስት የኢኮኖሚ ችግሮችን ለመፍታት የተገበረው ነው” ሲሉ የገንዘብ ሚንስትር ድኤታ ዶ/ር እዮብ ተካልኝ ከአሜሪካ ድምጽ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ተናግረዋል፡፡
የኢትዮጵያ መንግስት የተለያዩ ድጎማዎችን በማድረግና የደሞዝ ማሻሽያ በማድረግ ማሻሽያውን ተከትሎ ያለውን የኑሮ ውድነት ለማረጋጋት እየሰራ ነው ይላሉ፡፡ የኑሮ ውድነቱን ለማረጋጋት የሚውል ከ200 ቢሊየን ብር በላይ ተጨማሪ በጀትም ለማስጸደቅ የፖርላማውን ስራ መጀመር በመጠባበቅ ላይ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡
የፋይናንስ ሚንስትር ድኤታው ከአሜሪካ ድምጽ ጋር በኢትዮጵያ ምጣኔ ሃብት ይዞታ፣ የዋጋ ግሽበት፤ ኢትዮጵያ ያለባትን የዓለም አቀፍ አበዳሪዎች እዳን ጨምሮ በተለያዩ ጉዳዮች ያደረጉት ቃለምልልስ የመጀመርያ ክፍል ከተያያዘው ድምጽ ይከታተሉ፡፡
Your browser doesn’t support HTML5