ዩናይትድ ስቴትስ በኢትዮጵያ ያሉ ግጭቶች በሰላም እንዲፈቱ ጥረቷን እንደምትቀጥል የአገሪቱ አምባሳደር ጥሪ አቀረቡ።
አምባሳደሩ ኧርቪን ማሲንጋ፣የዩናይትድስቴትስ ዓለምአቀፍ የልማት ተራድኦ ድርጅት በምህጻሩ የዩኤስኤአይዲ የአምስት ዓመት “የኢትዮጵያ ድጋፍ ፕሮግራም” ማጠቃለያ ዝግጅት ላይ ባደረጉት ንግግር፣ በኢትዮጵያ ያሉ ግጭቶች የአገሪቱ የኢኮኖሚ እድገት እንዲያሽቆለቁል ማድረግን ጨምሮ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች እና የማህበራዊ አገልግሎት ተቋማት ውድመት እንዲቀጥል ማድረጋቸውን ገልፀዋል፡፡
ግጭቶች ከሚያስከትሉት ጉዳት ለማገገም በርካታ ዓመታትን የሚወስድ በመሆኑ፣ በውይይት ሰላምን ለማውረድ መታተር እንደሚያስፈልግ አሳስበዋል፡፡