79ኛው የመንግሥታቱ ጉባዔ አራተኛ ቀን ውሎ

Your browser doesn’t support HTML5

79ኛው የመንግሥታቱ ጉባዔ አራተኛ ቀን ውሎ

በኒው ዮርክ እየተካሄደ ባለው የመንግሥታቱ ጉባዔ ከምሳ ሰዓት በፊት በነበረው የካሪቢያን ሀገራቶች፣ ታንዛኒያ፣ ሞልዶቫ፣ ክሮሺያ እና እስራኤል ለመንግሥታቱ ድርጅት ንግግር ካደረጉ ሀገራቶች መካከል ናቸው።

በዕለቱ ንግግራቸውን ያደረጉት የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔታኒያሁ ወደ መድረክ ሲወጡ በረከት ያሉ ታዳሚዎች አዳራሹን ለቀው ወጥተዋል። የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔታኒያሁ ‘ሀገሬ ጦርነት ውስጥ ባለችበት ወቅት ይኼንን ጉባዔ ለመታደም አላሰብኩም ነበር’ ያሉ ሲሆን ነገር ግን ባለፉት ቀናቶች የተለያዩ ዓለም መንግሥታት ሀገሬን ሲወርፉ እና በሀሰት ሲከሱ በዝምታ ማለፍ አልቻልኩም ብለዋል።

ኔታኒያሁ የሀማስ ሮኬት ማስወንጨፍ አቅም 90 ከመቶ አውድመናል ያሉ ሲሆን። ዜጎቻችን ወደቤታቸው ሲመለሱ እና ሀማስ እጅ ሲሰጥ ጦርነቱ ያበቃል ብለዋል። በተመሳሳይ ሄዝቦላን ለማጥፋት እስራኤል ዘመቻዋን አጠናክራ ትቀጥላለች ሲሉ ተናግረዋል።

የዛሬው መርሃግብር ከመሪዎቹ ጉባዔ እና ንግግር ጎን ለጎን በመንግሥታቱ ድርጅት ዋና ጸሃፊ አንቶኒዮ ጉተሬዥ ተነሳሽነት የተመሰረተው ‘የወደፊቱ ጉባዔ’ ወይም ብሩህ ተስፋ የተሰኘው ዓለም አቀፍ የቃል ኪዳን ሥምምነትን ለማጠናከር መደረግ ስላለባቸው ተግባራዊ እርምጃዎች ውይይት እየተካሄደ ይገኛል። ወጣቶችን በውሳኔ ሰጭነት ማሳተፍ፣ የአየር ንብረት ለውጥን ጨምሮ በተለያዩ ሰብዓዊ መብት ጉዳዮች ላይ ዘላቂ ለውጥ ያለመ በሀገራት የጸደቀ ስምምነት መሆኑን የመንግሥታቱ ድርጅት አስታውቋል።

ዛሬ ከሰዓት በሚኖረው መርሃ ግብር ከምሥራቅ አፍሪካ ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ ንግግራቸውን እንደሚያደርጉ ይጠበቃል።