የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ከፍተኛ አመራር አባል ጃል ሰኝ ነጋሳ ከድርጅቱ መነጠላቸውን አስታወቁ

የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ከፍተኛ አመራር አባል ጃል ሰኝ ነጋሳ፣ ጃል መሮ(ኩምሳ ድሪባ)

Your browser doesn’t support HTML5

የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ከፍተኛ አመራር አባል ጃል ሰኝ ረጋሳ ከድርጅቱ መነጠላቸውን አስታወቁ

በጃል መሮ ወይም ኩምሳ ድሪባ ከሚመራው የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ራሳችንን አግልለናል ሲሉ የድርጅቱ የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባልና የማዕከላዊ ዞን የቀድሞ አዛዥ ጃል ሰኝ ነጋሳ አስታውቀዋል።

ጃል ሰኝ ነጋሳ መሆናቸውን ያስተዋወቁት የድርጅቱ አመራር፣ ከተመረጡ መገናኛ ብዙሀን ዘጋቢዎች በስልክ ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች የት እንደሆኑ ባልተገለፀ ቦታ ሆነው በሰጡት ምላሽ፣ ረቡዕ መስከረም 15 ቀን 2017 ዓ/ም የወጣውና የማዕከላዊ ዞን ዕዝ፣ በጃል መሮ ወይም ኩምሳ ድሪባ ከሚመራው ቡድን መለየቱን የሚገልፀው መግለጫ፣ የእሳቸውና የቡድናቸው መሆኑንም ጠቅሰዋል።

በኦሮሚያ የቀጠለውን ግጭት በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ዝግጁ ነን ሲሉም ጃል ሰኝ ትናንት መሰከረም 16 ቀን 2017 በሰጡት በዚሁ መግለጫ ተናግረዋል።

በጉዳዩ ላይ ከኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት አዛዥ ጃል መሮ ወይም ኩምሳ ድሪባ እና ባልደረቦቻቸው ምላሽ ለማግኘት ያደረግነው ጥረት ለጊዜው አልተሳካም።