ወደፍሎሪዳ በከፍተኛ ፍጥነት በማምራት ላይ ያለችው ሃሪኬይን ሄለን ከባድ አደጋ ደቅናለች

  • ቪኦኤ ዜና

ከባድ ዝናብ ይዛ በሜክሲኮ ባህረ ሰላጤ በከፍተኛ ፍጥነት  እየተጓዘች ያለችው ሃሪኬን ሄለን የዩናይትድ ስቴትስ ፍሎሪዳ ግዛት በማቅናት ላይ መሆኗን የዩናይትድ ስቴትስ ብሔራዊ የሃሪኬን ክትትል ማዕከል አስታወቀ፡፡

ከባድ ዝናብ ይዛ በሜክሲኮ ባህረ ሰላጤ በከፍተኛ ፍጥነት እየተጓዘች ያለችው ሃሪኬን ሄለን የዩናይትድ ስቴትስ ፍሎሪዳ ግዛት በማቅናት ላይ መሆኗን የዩናይትድ ስቴትስ ብሔራዊ የሃሪኬን ክትትል ማዕከል አስታወቀ፡፡ በአንድ አካባቢዎች እስከ ስድስት ሜትር ከፍታ ያለው ለሕይወት አደገኛ የሆነ ዝናብ ሊያስከትል እንደሚችል ማዕከሉ አመልክቷል፡፡

በሜክሲኮ ባሕረ ሰላጤ አድርጋ በሰዓት 155 ኪሎ ሜትር ፍጥነት ባለው ኅይለኛ አውሎ ንፋስ የምትውዘገዘገው ኽሪኬን ሄለን ዛሬ ሐሙስ ማታ ወይም ዓርብ ማለዳ ፍሎሪዳ ግዛት እንደምትደርስ ይጠበቃል፡፡ ለህይወት እጅግ አደገኛ የሆነ ጎርፍ እና በከፍታ አካባቢዎች የመሬት መንሸራተት ሊከሰት እንደሚችል ተጠርጥሯል፡፡

የፍሎሪዳ አገረ ገዢ ሮን ደ ሳንቲስ ማያሚ ዴድን ጨመሮ በ67ቱም ግዛቶች አስቸኳይ ጊዜ አውጀዋል፡፡ የብሔራዊ ዘብ አባላቱንም እርዳታ ለመስጠት በተጠንቀቅ እንዲጠባበቅ አንቀሳቅሰዋል፡፡

ፕሬዚደንት ጆ ባይደን ትላንት ረቡዕ ገለጻ የተደረገላቸው ሲሆን አስተዳደራቸው ለፍሎሪዳ እና ለሌሎቹም በከባድ አውሎ ንፋስ እና ዝናቡ መስመር ላይ ለሚገኙ ግዛቶች እርዳታ ለመስጠት ዝግጁ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡