የፍልሥጥኤማዊያን ደጋፊዎች የተቃውሞ እንቅስቃሴ ካማላ ሐሪስን ሚሺጋን ላይ ይጎዳቸው ይሆን?

  • ቪኦኤ ዜና

Michigan Gaza Vote

Your browser doesn’t support HTML5

የፍልሥጥኤማዊያን ደጋፊዎች የተቃውሞ እንቅስቃሴ ካማላ ሐሪስን ሚሺጋን ላይ ይጎዳቸው ይሆን?

ፕሬዚደንት ጆ ባይደንን የጋዛ ጦርነትን በሚመለከት የሚከተሏቸውን ፖሊሲዎች በመቃወም የጀመረው The Uncommited National Movement ማንን እንደሚመርጡ ያልወሰኑ መራጮች ብሔራዊ ንቅናቄ የተባለው ተቃውሞ ለዲሞክራቲክ ፓርቲው እጩዋ ለምክትል ፕሬዚደንት ካምላ ሐሪስ ድጋፋቸውን እንደማይሰጡ ባለፈው ሳምንት አሳውቀዋል፡፡

“Abandon Harris” ሐሪስን እንዳትደግፉ በሚል ስም የተሰባሰበው ሌላው የፍልስጥኤማውያን ደጋፊ ስብስብ ደግሞ ካማላ ሐሪስ በምርጫው እንዲሸነፉ በመሥራት መሆኑን አስታውቋል፡፡ ታዲያ እነዚህ ንቅናቄዎች ሪፐብሊካኖች እና ዲሞክራቶች በተቀራረበ ድጋፍ በሚፋለሙባቸው ክፍለ ግዛቶች የምርጫ ውጤቶች ላይ አንድምታ ይኖራቸው ይሆን?

የአሜሪካ ድምጽ የኋይት ሐውስ ቢሮ ዋና ዘጋቢ ፓትሲ ዊዳኩስዋራ ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ ከማናቸውም ብዛት ያላቸው አረብ አሜሪካዊያን ከሚኖሩባት ከሚሺጋን ተከታዩን አድርሳናለች፡፡