በኢትዮጵያ ከ9 ሺህ በላይ ስደተኞች ዲጂታል መታወቂያ ማግኘታቸው ተገለፀ

የስደተኞች እና ተመላሾች አገልግሎት

Your browser doesn’t support HTML5

በኢትዮጵያ ከ9 ሺህ በላይ ስደተኞች ዲጂታል መታወቂያ ማግኘታቸው ተገለፀ

ባለፉት 6 ወራት ውስጥ በኢትዮጵያ የሚገኙ 10 ሺህ የሚጠጉ ስደተኞች ፋይዳ የተሰኘ ዲጂታል መታወቂያ እነደተሰጣቸው የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽነር፣ በምህጻሩ ዩ.ኤን.ኤች.ሲ.አር አስታውቋል።

ዲጂታል መታወቂያው፣ ስደተኞች የተለያዩ ማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ እንዲሁም የደኅንነት አገልግሎቶችን እንዲያገኙ እንደሚያስችል ተቋሙ ገልጿል።

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰማኮ) ተጠባባቂ ዋና ኮሚሽነር ራኬብ መሰለ፣ተመዝግበው እውቅና ማግኘት አለመቻል በተለይ የከተማ ስደተኞችን ለእስር እና መሰል ችግሮች አጋልጧል ሲሉ በቅርቡ ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል።

በሂደቱ ላይ መዘግየት መታየቱን የገለፁት በኢትዮጵያ መንግሥት የስደተኞች እና ተመላሾች አገልግሎት የስደተኛች ከለላ ዳይሬክተር ዳባ ለሜሳ፣ ለዚህ ምክንያቱ የባለሙያዎች እጥረት እንደሆነ ጠቁመዋል ፡፡ በአሁኑ ወቅት ችግሩን ለመቅረፍ ከዩ.ኤን.ኤች.ሲ.አር ጋራ በመተባበር፣ አገልግሎቱን የሚሰጡ ባለሙያዎች ሰልጥነው በየካምፖች እንዲሰማሩ ማድረጋቸውንም አስረድተዋል፡፡