የመንግስታቱ ድርጅት ‘ብሩህ ተስፋ’ የተሰኘ በሰብዓዊነት ላይ ያተኮረ ስምምነት አጸደቀ

የመንግስታቱ ድርጅት ቢሮ ኒውዮርክ መስከረም 2016 ዓ.ም

የመንግስታቱ ድርጅት በ21ኛው መቶ ክፍለ ዘመን በሰውልጆች ላይ የተጋረጡትን የአየር ንብረት ለውጥ እና የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን ጨምሮ፤ በአለም ዙሪያ እየንሰራፉ ያሉ ተግዳሮቶችን ለመፍታት ያለመ ‘የወደፊት ስምምነት’ ዛሬ እሁድ አጽድቋል። ስምምነቱ ከመፈረሙ ከደቂቃዎች በፊት ከሩሲያ ተቃውሞ ገጥሞት ነበረ።

"የወደፊቱን ጉባዔ" አዘጋጅ የሆኑት የመንግስታቱ ድርጅት ዋና ጸሃፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዥ፤ ዓለም አቀፍ ትብብርን በማደስ የሰውን ልጅ ታሪክ ለመቅረጽ “በትውልድ አንዴ የሚገኝ ዕድል” በማለት ነው መምሪያው እንዲጸድቅ ያቀረቡት።

የፊታችን ማክሰኞ ለሚጀመረው የተባበሩት መንግስታት ጠቅላላ ጉባዔ ላይ ለመሳተፍ የተሰባሰቡ በደርዘን የሚቆጠሩ የሀገር እና የመንግስት መሪዎች በፊርማ ስነስርዓቱ ላይ ተሳትፈዋል።