በደቡብ ወሎ ዞን ለተረጂዎች ርዳታ ዘግይቷል ተባለ

ፎቶ ፋይል፦ ደሴ

Your browser doesn’t support HTML5

በደቡብ ወሎ ዞን ለተረጂዎች ርዳታ ዘግይቷል ተባለ

የደቡብ ወሎ ዞን አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ጽ/ቤት በዞኑ ለሚገኙ ተፈናቃዮች የእለት ደራሽ ምግብ በወቅቱ ለማቅረብ መቸገሩን ስለመግለጹ፡፡

በኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች ተቀስቅሶ በነበረ የጸጥታ ስጋት ምክንያት ተፈናቅለው በአማራ ክልል ደቡብ ወሎ ዞን ውስጥ ለሚኖሩ ሰዎች የምግብ ርዳታ በወቅቱ ለማቅረብ መቸገሩን የዞኑ አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ጽ/ቤት አስታወቀ፡፡

መምሪያው እንደገለጸው የምግብ ርዳታውን ለማቅረብ የተቸገረው ከፌደራል መድረስ ያለበት የምግብ ድጋፍ በመዘግየቱ ነው፡፡

የኢትዮጵያ አደጋ ስጋት አመራር በበኩሉ መጠነኛ መዘግየት የሚፈጠሩት በአንዳንድ አካባቢዎች በሚፈጠሩ የጸጥታ ችግሮችና የትራንስፖርት እጥረት ምክንያት እንንሆነ ገልጾ በቅርቡ ለማከፋፈል ጥረት ይደረጋል ብለዋል፡፡

የአሜሪካ ድምጽ ያናገራቸውና ተፈናቅለው በመጠለያ ውስጥ የሰፈሩ ሰዎች በበኩላቸው በምግብ አቅርቦት እጥረቱ ምክንያት ህጻናት ለልመና እየተዳረጉ መሆኑን አመልክተዋል፡፡