ዋነኛ ቡና ላኪ ሃገራት ምርት መቀነስ ለኢትዮጵያ ቡና አለም አቀፍ ሽያጭ እድልን ፈጥሯል ተባለ

Coffee History

Your browser doesn’t support HTML5

ዋነኛ ቡና ላኪ ሃገራት ምርት መቀነስ ለኢትዮጵያ ቡና አለም አቀፍ ሽያጭ እድልን ፈጥሯል ተባለ

ኢትዮጵያ በሃምሌና ነሃሴ ወር ከፍተኛ የቡና ሽያጭ ገቢ ማግኘቷ ተገለጸ፡፡ የኢትዮጵያ ቡና እና ሻይ ባለስልጣን ባወጣው መግለጫ እንዳስታወቀው በሁለት ወራት ከተሸጠው ከ82ሽህ ቶን በላይ ቡና ካልፈው አመት ጋር ሲነጻጸር ከፍተኛ ያለው 377 ሚሊየን ዶላር ገቢ ተገኝቷል ብሏል፡፡

የኢትዮጵያ ቡና ማኅበር ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ግዛት ወርቁ በበኩላቸው አለም አቀፍ የቡና ገበያ ዋጋ ጭማሪ ማሳየቱን ገልጸው ዋነኛ ቡና ላኪ የሆኑ እንደ ብራዚል ያሉ ሃገራት ምርት መቀነስ ለኢትዮጵያ ቡና አለም አቀፍ ሽያጭ እድልን ፈጥሯል ብለዋል፡፡