የማሊ ወታደራዊ ጁንታ የፈረንሳይኛ ቋንቋ ቴሌቪዥንን ለ3 ወር አገደ

ባማኮ፤ ማሊ

የማሊ ወታደራዊ ጁንታ ቲቪ ፋይቭ ሞንዴ (TV5 Monde) ተብሎ የሚጠራውን በፈረንሳይ ቋንቋ የሚያሰራጭ የቴሌቭዥን ጣቢያ ለሦስት ወራት አገደ፡፡

ገዥው የማሊ ወታደራዊ መንግሥት የቴሌቪዥን ጣቢያውን ያገደው በዜና ዘገባው ላይ “ሚዛናዊነት” የጎደለው በመሆኑ ነው ሲል መንግሥታዊው የመገናኛ ብዙኃን ተቆጣጣሪው መሥሪያ መግለጹን ኤኤፍፒ ዛሬ ረቡዕ የደረሰውን መግለጫ ጠቅሶ ዘግቧል፡፡

ከፍተኛ የኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ባለሥልጣን የቴሌቭዥን ጣቢያው በሰሜናዊቷ ቲንዛኦዋቴን ከተማ በሰው አልባ አውሮፕላኖች በተፈጸመ ጥቃት በጥቂቱ 15 ንፁሀን ዜጎች መሞታቸውን ሲዘግብ የማሊ ጦር ስለ ክስተቱ ያለውን አስተያየት አላካተተም ሲሉ ተችተዋል፡፡