ኢትዮጵያ በየአመቱ መስከረም ወር ላይ አዲስ አመትን የምትቀበልበት የራሷ የዘመን አቆጣጠር ያላት ሃገር ናት::
አስራ ሶስተኛ ወር የምትባለው ጳጉሜ ወርን ጨምሮ በቀንና አመታት አቆጣጠርም ከአውሮፖውያ የዘመን ቀመር በተለየ ትቆጠራለች::
የአሜሪካ ድምጽ የ2017 ዓ.ም አዲስ አመት መቃረብን ምክንያት በማድረግ በዚህ ርዕሰ ጉዳይ በርካታ መጽሃፍትን ያሳተሙትን የስነ ፈለክ ባለሙያ መጋቢ ሃዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰን አነጋግሯቸዋል::
የኢትዮጵያ የዘመን አቆጣጠር በተገቢው መንገድ ዓለም እዲያውቀው አልተደረገም የሚሉት ዶክተር ሮዳስ የዘመን ቀመሩ ለምን ልዩ እንደሆነና አቆጣጠሩን በተመለከተ ከአሜሪካ ድምጽ ጋር ቆይታ አድርገዋል::
Your browser doesn’t support HTML5