በትግራይ ክልል፣ 26 አባሎቼ እና አመራሮች በፖለቲካዊ እምነታቸው ምክንያት ታስረዋል ሲል ህወሓት ከሰሰ፡፡
በአወዛጋቢው የህወሓት 14ኛ ጉባኤ ምክትል ሊቀመንበር ሆነው የተመረጡት አቶ አማኑኤል አሰፋ፣ የህወሓት አባላት እና አመራሮች በፖለቲካዊ እምነትቸው ምክንያት እየታሰሩ፣ ከሥራም እየተባረሩ ናቸው ብለዋል፡፡ በጉዳዩ ላይ ከክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር አመራሮች ምላሽ ለማግኘት ያደረግነው ጥረት ለጊዜው አልተሳካም፡፡
ዛሬ አመሻሽ ላይ መግለጫ የሰጡት የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ምክትል ፕሬዝዳንት ሌፍተናንት ጀነራል ታደሰ ወረደ: በትግራይ ክልል በህወሓት አመራሮች መካከል ያለው ክፍፍል በተረጋጋ መንገድ ሲፈታ እየቀረበ ያለው የእስራት ቅሬታ መፍትሄ ያገኛል ብለዋል፡፡ ታስረዋል ስለተባሉ 26 ሰዎች ግን ዝርዝር መረጃ እንደሌላቸው ገልጸዋል፡፡
Your browser doesn’t support HTML5