ሱዳን ሰላማዊ ዜጎችን ለመጠበቅ የመንግስታቱ ድርጅት ያደረገውን ‘የገለልተኛ’ ሃይል ጥሪ አልቀበልም አለች

የሱዳን ተፈናቃዮች ነሐሴ 2016 ዓ.ም

ከአንድ ዓመት በላይ በዘለቀው የሱዳን ጦርነት ሳቢያ ከቤታቸው የተፈናቀሉትን በሚሊዮን የሚቆጠሩ ንፁሀን ዜጎች ከለላ ለመስጠት “ራስ አገዝ እና ገለልተኛ ሃይል” እንዲሰማራ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ባለሙያዎች ያቀረቡትን ጥሪ ውድቅ ሱዳን አድርጋለች።

ካለፈው ሚያዚያ ወር አንስቶ በሱዳን የተቀሰቀሰው ግጭት ሰራዊቱ በፓርላማ ከጸደቀው የመንግስቱ ወታደራዊ ሃይሎች ጋር በማጋጨት በብዙ አስር ሺዎች መሞት መንስዔ መሆንን ጨምሮ በዓለም ካሉ አስከፊ ሰብዓዊ ቀውሶች አንዱን አስከትሏል።

በጄኔራል አብዱልፈታህ አል ቡርሃን ለሚመራው ጦር ታማኝ የሆነው የሱዳን ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፤ ቅዳሜ ማምሻው ላይ በሰጠው መግለጫ “የሱዳን መንግስት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ተልዕኮ የሚያቀርበውን ሃሳብ ሙሉ በሙሉ ውድቅ ያደርጋል” ብሏል።

የዓለም ጤና ድርጅት ሃላፊ ቴዎድሮስ አድሃኖም እሁድ እለት ሱዳንን በጎበኙበት ወቅት "የአደጋው መጠን አስደንጋጭ ነው፣ ግጭቱን ለመግታትና እያደረሰ ያለውን ስቃይ ምላሽ ለመስጠት በቂ እርምጃ እየተወሰደ አይደለም" ሲሉ ተናግረዋል።

የሱዳን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መግለጫ በቡርሃን የቀድሞ ምክትል፤ መሀመድ ሃምዳን ዳጋሎ የሚመራው የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ሃይል “ሲቪሎችን እና ሲቪል ተቋማትን ስልታዊ በሆነ መንገድ ዒላማ አድርጓል” ሲል ከሷል።