የኤሌክትሪክ አገልግሎት ክፍያ፣ በየሦስት ወሩ ሊጨመር ነው

አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ

Your browser doesn’t support HTML5

የኤሌክትሪክ አገልግሎት ክፍያ፣ በየሦስት ወሩ ሊጨመር ነው

መንግሥታዊው የኤሌክትሪክ ኃይል አቅራቢ ተቋም የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት፣ ከመጪው መስከረም ወር ጀምሮ በየሶስት ወሩ፣ በአገልግሎት ክፍያ ላይ ጭማሪ እንደሚያደርግ አስታወቀ፡፡ የተቋሙ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ኢንጅነር ሽፈራው ተሊላ፣ በትላንትናው ዕለት በሰጡት መግለጫ፣ አዲሱ የአገልግሎት ክፍያ ጭማሪ ለሚቀጥሉት አራት ዓመታት እንደሚቆይ ተናግረዋል፡፡

በክፍያ ማስተካከያው፣ ከ50 እስከ 200 ኪሎዋት የኤሌክትሪክ ኃይል የሚጠቀሙ አብዛኞቹ ደንበኞች ድጎማ ይደረግላቸዋል ብለዋል፡፡ በጉዳዩ ላይ ለአሜሪካ ድምፅ አስተያየት የሰጡት የኢኮኖሚ ባለሙያው ዶ/ር አቡሌ መሐሪ በበኩላቸው፣ ውሳኔ ጊዜውን የጠበቀ አይደለም። ህዝቡን ለከፍተኛ የኑሮ ጫና የሚዳርግ ነው ይላሉ፡፡