ድንበር የለሽ የሐረር ልጆች ማህበር በትውልድ ከተማቸው ሐረር ያሉ ወገኖቻቸውን ለመርዳት ባሰቡ የሰሜን አሜሪካ ነዋሪ የከተማዋ ተወላጆች የተመሰረተ ነው፡፡
ካለፉት ዓመታት ጀምሮ በሐረር ያለውን የንጹህ የመጠጥ ውሃ እጥረትን ጨምሮ በትምህርት ቤቶች ተማሪዎች ያለባቸው የትምህርት ቁሳቁስ ችግር ከአባላቱ በሚያሰባስበው ገንዘብ እየደገፈ እንደሚገኝ የማህበሩ ፕሬዳንት ዶክተር ማሾ አብርሃ ይናገራሉ፡፡
ባለፈው ዕሁድ እውቁ ተዋናይ አለማየሁ ታደሰን አምባሳደር አድርጎ የሰየመበት የማህበሩ አራተኛ የገቢ ማሰባሰቢያ የእራት ምሽት ቨርጂኒያ አሌክሳንድሪያ ውስጥ ተካሂዷል፡፡
ለኢትዮጵያውያን በአሜሪካ ቅንብራችን የተዘጋጀውን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ይመልከቱ፡፡