ዓለም አቀፉ የሰብአዊ መብቶቶች ድርጅት ሂዩማን ራይትስ ዎች የሊባኖስ ጦር እና በአቅራቢያው ቆጵሮስ የሚገኙ ባለሥልጣናት ፍልስተኞች ወደ አውሮፓ እንዳይደርሱ በማድረግ በጦርነት ወደ ታመሰችው ሶሪያ መልሰው በማባረር በጋራ እየሰሩ ነው ሲል ከሰሰ፡፡
የሊባኖስ ጦር በጀልባ ለመውጣት የሚሞክሩትን ሶሪያውያን ስደተኞችን “ ይዞ በመመለስ ወዲያውኑ ወደ ሶሪያ እንዳሚያባርራቸው” የመብት ተሟጋቹ ድርጅት ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።
የባህር ዳርቻ ጠባቂዎችን ጨምሮ የቆጵሮስ የጸጥታ ኃይሎች ጀልባቸው ቆጵሮስ የደረሰች ስደተኞችን የስደት ህጋዊ ሁኔታ ሳያለይ ወይም ወደ ሶሪያ ተመልሰው የመላካቸው ስጋት ባለበት ሁኔታ ሶሪያውያኑን ወደ ሊባኖስ መልሰው ልከዋቸዋል” ሲል ድርጅቱ ከሷል፡፡
“ከቆጵሮስ ወደ ሊባኖስ የተመለሱ አብዛኞቹ ፍልስተኞች ወደ በሊባኖስ ጦር ወደ ሶሪያ ተመልሰው ተባረዋል” ሲል ድርጅቱ አክሎ ገልጿል፡፡
ኤኤፍፒ ስለሂዩማን ራይት ዋች ክስ የቆጵሮስ ባለሥልጣናትን አስተያየት አላገኘም፡፡
እኤአ ከ2019 መጋባደጃ አንስቶ ከባድ የኢኮኖሚ ቀውስ ያጋጠማት ሊባኖስ ወደ ሁለት ሚሊዮን የሚጠጉ ሶሪያውያን ስደተኞችን ታስተናግዳለች፡፡
እኤአ በ2011 የተቀሰቀሰው የሶሪያ ጦርነት ከግማሽ ሚሊዮን በላይ ሰዎችን ሲገድል ከጦርነቱ በፊት ከነበረው ህዝብ ግማሽ ያህሉን አፈናቅሏል።